መሳፍንት 5:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጉርጉር ልብስ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣ እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን? ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶች ለሲሣራ ደርሰውት፣ በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለዐንገቴ ይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምርኮ አግኝተው በመካከላቸው እየተከፋፈሉ አይደለምን? አንድ ወይም ሁለት ቈነጃጅት ለያንዳንዱ ወንድ፥ ለሲሣራ በልዩ ልዩ ቀለማት ያጌጠ የልብስ ምርኮ፥ ለእኔም ለአንገቴ በአንገቴ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጒርጒር ልብስ፥” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምርኮውን ሲካፈል፥ በኀያላኑም ቸብቸቦ ላይ ወዳጆችን ሲወዳጅ ያገኙት አይደለምን? የሲሣራ ምርኮ በየኅብሩ ነበረ፤ የኅብሩም ቀለም የተለያየ ነበረ፤ የማረከውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአንገቱ ላይ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጕርጉር ልብስ። |
ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር።
ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ።
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።