Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 13:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ ጌጠኛ የሆነና በዚያ ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን ዐይነት ልብስ ለብሳ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18-19 ትዕማርም የአምኖን አሽከር ከቤት አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ዘመን ያላገቡ የነገሥታት ልጆች ይለብሱት የነበረውን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር፤ እርስዋም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳ እጅዋን በራስዋ ላይ በመጫን ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ብዙ ኅብር ያለ​ው​ንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የን​ጉሡ ልጆች ደና​ግሉ እን​ዲህ ያለ​ውን ልብስ ይለ​ብሱ ነበ​ርና፤ አገ​ል​ጋ​ዩም አስ​ወ​ጥቶ በሩን ዘጋ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና፥ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 13:18
7 Referencias Cruzadas  

“ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጉርጉር ልብስ።”


እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።


ብዙ ኅብር ያለበትንም ልብሱን ወደ አባታቸው ወስደው “እነሆ፥ ይህን አገኘን የልጅህ ልብስ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ እይ” አሉት።


እንዲህም ሆነ፥ ዮሴፍም ወደ ወንድሞቹ በቀረበ ጊዜ የለበሳትን በብዙ ኅብር ያጌጠቺቱን ቀሚሱን ገፈፉት፥


ከዚያም በኋላ ኤሁድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው።


ወጣት አገልጋዩንም ጠርቶ፥ “ይህቺን ሴት ከፊቴ አስወጣና በሩን ዝጋባት” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios