Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 5:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ነገሥታት መጡ፥ ተዋጉም፥ በዚያ ጊዜ በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፥ የብር ዘረፋም አልወሰዱም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤ ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በመጊዶ ውሃ አጠገብ በታዕናክ፥ ነገሥታቱ መጥተው ተዋጉ፤ ከዚያም የከነዓንን ነገሥታት ተዋጉ፤ የብር ምርኮ አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ነገሥታት መጡ፥ ተዋጉም፥ በዚያ ጊዜ በመጊዶ ውኆች አጠገብ በታዕናክ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፥ የብር ዘረፋም አልወሰዱም።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:19
19 Referencias Cruzadas  

አብራምም የሰዶምን ንጉሥ አለው፦ ሰማይንና ምድርን ወደሚገዛ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጄን ከፍ አድርጌአለሁ፥


ከዚያም ቃየን ከጌታ ፊት ወጣ፥ ከዔድንም በስተ ምሥራቅ፥ በኖድም ምድር ተቀመጠ።


በዓና የተባለው የአሒሉድ ልጅ፦ የታዕናክና የመጊዶ ከተሞች፥ እንዲሁም በቤት ሻን አጠገብ ያለው ግዛት በሙሉ፥ በጻርታን ከተማ አጠገብ ያለው ግዛትና በኢይዝራኤል ከተማ በስተ ደቡብ ያለው ግዛት፥ እንዲሁም አቤልመሖላና ዮቅመዓም ተብለው እስከሚጠሩት ከተሞች ድረስ ያለው ግዛት ሁሉ አስተዳዳሪ።


በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤


ኢዮስያስ ግን ማንነቱን ሸሽጎ ለመዋጋት ወጣ እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በጌታም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፥ በመጊዶም ሸለቆ ለመዋጋት መጣ።


እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥ ወደ አሕዛብም በተንኸን።


የታዕናክ ንጉሥ፥ የመጊዶ ንጉሥ፥


በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ ይብልዓምና መንደሮችዋ፥ ዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ዓይነዶርና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ታዕናክና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ መጊዶና የመንደሮችዋ ሰዎች፥ ሦስቱ ኮረብቶች ለምናሴ ነበሩ።


በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።


በፈረሱም የተቀመጠውንና ሠራዊቱን ይወጉ ዘንድ አውሬውና የምድር ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ተሰብስበው አየሁ።


የምናሴ ነገድ ግን በቤትሳን፥ በታዕናክ፥ በዶር፥ በይብለዓም፥ በመጊዶንና በየአካባቢያቸው ያሉት መንደሮች ነዋሪውን ሕዝብ ስላላስወጡ፥ ከነዓናውያን ኑሮአቸውን በዚያው ለማድረግ ወሰኑ።


ዘጠኝ መቶ የብረት ሠረገሎችንና ከሐሮሼት ሐጎይም እስከ ቂሶን ወንዝ ያለውን ሠራዊቱን በሙሉ አሰባሰበ።


“ምርኮ አግኝተው የለምን? ተካፍለውስ የለምን? ለእያንዳንዱ ሰው ምርኮ አንዲት ወይም ሁለት ቈነጃጅት፥ ለሲሣራ ምርኮ ልዩ ልዩ ያለው ልብስ፥ በአንገትጌ ላይ በሁለት እጥፍ የተጠለፈ ዝንጉርጉር ልብስ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos