“አምላካችሁ ጌታ ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በጌታና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል።
መሳፍንት 4:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያች ዕለት እግዚአብሐር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤላውያን ፊት እንዲሸነፍ አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት እግዚአብሔር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤላውያን ፊት እንዲሸነፍ አደረገው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በዚያን ቀን እስራኤላውያን በከነዓናዊው ንጉሥ በያቢን ላይ ድልን እንዲቀዳጁ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢንን በእስራኤል ልጆች ፊት አዋረደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግዚአብሔር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤል ልጆች ፊት አዋረደ። |
“አምላካችሁ ጌታ ከእናንተ ጋር አይደለምን? በምድርም የሚቀመጡትን በእጄ አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ምድርም በጌታና በሕዝቡ ፊት ተገዝታለችና በዙሪያችሁ ሁሉ ዕረፍትን ሰጥቶአችኋል።
ልጆቹም ገብተው ምድሪቷን ወረሱ፤ የምድሪቱን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው ደመሰስካቸው፥ የወደዱትን ነገር እንዲያደረጉባቸው ከነገሥታቶቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋር በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው።
ባራቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፥ ያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ።