መሳፍንት 20:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማይቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፥ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላይቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የጢሱ ዐምድ ከከተማዪቱ መነሣት በጀመረ ጊዜ፣ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ዞረው የመላዪቱ ከተማ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ምልክቱ ታየ፤ ይኸውም ጢሱ እንደ ደመና ሆኖ እየተትጐለጐለ ወደ ላይ ይወጣ ነበር፤ ብንያማውያንም ወደኋላቸው ሲመለከቱ ከተማይቱ በሙሉ በእሳት ተያይዛ ነበልባሉ ወደ ላይ ሲወጣ አዩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምልክቱም በጢሱ ዐምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደኋላቸው ተመለከቱ፤ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምልክቱ በጢሱ ዓምድ ከከተማው ሊወጣ በጀመረ ጊዜ ብንያማውያን ወደ ኋላቸው ተመለከቱ፥ እነሆም፥ የሞላ ከተማው ጥፋት ወደ ሰማይ ወጣ። |
የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሸው ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ስለ ተመለሱ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም።
በዚያች ምሽት ከኰረብታማው ከኤፍሬም አገር መጥቶ በጊብዓ የሚኖር አንድ መጻተኛ ሽማግሌ ከዕርሻ ሥራው መጣ፤ የዚያ አገር ሰዎች ግን ብንያማውያን ነበሩ።