ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
መሳፍንት 20:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፥ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፣ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደ ገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ሰዎች ገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ብንያማውያን በሁለተኛው ቀን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚህም ጊዜ ዐሥራ ስምንት ሺህ የሠለጠኑ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ገደሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ቀን የብንያም ልጆች ሊገጥሙአቸው ከገባዖን ወጡ፤ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎችን በምድር ላይ ገደሉ፤ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ቀን ብንያም ከጊብዓ በእነርሱ ላይ ወጣ፥ ከእስራኤልም ልጆች ደግሞ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ፥ እነዚህም ሁሉ ሰይፍ የሚመዝዙ ነበሩ። |
ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
ነገር ግን ዐመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያጎላ ከሆነ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በቁጣ ቢቀጣን ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው እላለሁ።
የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በጌታ ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።