ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት።
መሳፍንት 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በችቦዎቹ ላይ እሳት በማቀጣጠል ቀበሮዎቹን ገና ወዳልታጨደው ወደ ፍልስጥኤማውያን የስንዴ ሰብል ውስጥ ለቀቃቸው፤ በዚህም ዐይነት ታጭዶ የተከመረውን ብቻ ሳይሆን ገና በማሳ ላይ ያለውን ስንዴ፥ የወይራና የወይን ተክል ጭምር አቃጠለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፤ ነዶውንም፥ ክምሩንም፥ የቆመዉንም እህል፥ ወይኑንም፥ ወይራዉንም አቃጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፥ ነዶውንም የቆመውንም እህል ወይኑንም ወይራውንም አቃጠለ። |
ከዚያም አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ “ተመልከቱ፥ የኢዮአብ እርሻ የሚገኘው ከእኔ እርሻ አጠገብ ነው፤ በእርሻው ላይ የገብስ ሰብል አለው፤ ሄዳችሁም እሳት ልቀቁበት” አላቸው። ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች ሄደው እርሻውን በእሳት አቃጠሉት።
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ።
ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋር አሰረው።
ፍልስጥኤማውያን፥ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፥ “ሚስተ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የቲምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው።