መሳፍንት 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ፍልስጥኤማውያን፥ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፥ “ሚስተ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የቲምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ፍልስጥኤማውያን፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ሚስቱ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የተምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ፍልስጥኤማውያንም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የቴምናታዊዉ አማች ሶምሶን ነው” አሉአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ወጥተው የአባቷን ቤትና እርስዋን አባቷንም በእሳት አቃጠሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ፍልስጥኤማውያንም፦ ይህን ያደረገው ማን ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የተምናዊው አማች ሶምሶን ነው አሉ። ፍልስጥኤማያንም ወጥተው ሴቲቱንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ። Ver Capítulo |