ዘፀአት 23:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱን ሳትጠቀምባትና ሳታርሳት እንዲሁ ተዋት፤ ከዚያም በወገንህ መካከል ያሉት ድኾች ከርሷ ምግብ ያገኛሉ፤ የዱር አራዊትም ከእነርሱ የተረፈውን ይበላሉ። በወይን ቦታህና በወይራ ዛፎችህም ላይ እንዲሁ አድርግ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል የሚገኙ ድኾች ምግብ ያገኙ ዘንድ በምድሪቱ ላይ ምንም ነገር አታምርት፤ ምድሪቱ ታርፍ ዘንድ ተዋት፤ ከእነርሱ የተረፈውንም የምድር አራዊት ይመገቡት፤ የወይን ተክል ቦታህንና የወይራ ዘይት ዛፎችህንም እንደዚሁ አሳርፋቸው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ። Ver Capítulo |