በዚህ ጊዜ ዮናታንና አሒማዓጽ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዔንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።
ኢያሱ 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ወገን በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸው ድንበር ከራፋይም ሸለቆ በስተሰሜን ባለው በሄኖም ሸለቆ ትይዩ ቍልቍል ወደ ኰረብታው ግርጌ ይወርዳል፤ ከዚያም ከኢያቡሳውያን ከተማ በደቡብ በኩል ባለው ተረተር አድርጎ ወደ ሄኖም ሸለቆ በመውረድ እስከ ዓይንሮጌል ይዘልቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ድንበሩ የሔኖም ልጅ ሸለቆ ትይዩ ወደ ሆነው ተራራ ግርጌ ይወርዳል፤ እርሱም ከራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ከዚያም ወደ ሔኖም ሸለቆ ይወርድና በኢያቡሳውያን ተረተር ጐን አድርጎ ወደ ኤንሮጌል ይደርሳል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበሩም በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፤ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምንጭም ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳለው ተራራ መጨረሻ ወረደ፥ እርሱም በራፋይም ሸለቆ በሰሜን በኩል ነው፥ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያቡስ ዳር በደቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ዓይንሮጌልም ወረደ። |
በዚህ ጊዜ ዮናታንና አሒማዓጽ ወደ ከተማዪቱ ከገቡ ስለሚታዩ በዔንሮጌል ይጠባበቁ ነበር፤ አንዲት ልጃገረድ አገልጋይ ወደዚያ እየሄደች በምትነግራቸው ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ ይህንኑ ወስደው ለንጉሥ ዳዊት ይነግሩት ነበር።
አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዔንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይጋ ሠዋ፥ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባርያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ።
ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት በማቃጠል እንደ መሥዋዕት አቀረበ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፥ አስማትም አደረገ፥ መተተኛም ነበረ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ጌታንም ለማስቈጣት በጌታ ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪው ዕቃ እንደሚሰባበር ዳግመኛም ሊጠገን እንደማይችል፥ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ ሌላ የለምና በቶፌት ይቀበራሉ።
ይሁዳን ኃጢአት ለማሠራት፥ ይህን ርኩሰት እንዲያደርጉ ባላዛቸውም በልቤም ባላስበውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሌክ በእሳት ለመሠዋት፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ጼላ፥ ኤሌፍ፥ ኢየሩሳሌም የምትባል ኢያቡስ፥ ጊብዓና ቂርያትይዓሪም፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
ነገር ግን የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ አላስወጧቸውም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋር በዚያ አብረው ይኖራሉ።
ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ።