ኢያሱ 15:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፤ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽዓራይም፣ ዓዲታይም፣ ግዴራ፣ ግዴሮታይም ናቸው፤ ከተሞቹም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሻዕራይም፥ ዐዲታይም፥ ገዴራና ገዴሮታይም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቃርም፥ ጋዴርና ሰፈሮችዋ፥ ዐሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥ ሽዓራይም፥ ዓዲታይም፥ ግዴራ፥ ግዴሮታይም፥ አሥራ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ከዚህ በኋላ የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች ተነሥተው እየፎከሩ ፍልስጥኤማውያንን እስከ ጋት መግቢያና እስከ ዔቅሮን በሮች ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያንም ሬሳ ከሸዓራይም አንሥቶ እስከ ጋትና ከዚያም እስከ ዔቅሮን በሮች ባለው መንገድ ላይ ወደቀ።