La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 11:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ፥ በቍጥር ም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ከሚሆን ብዙ ሕዝብ፥ እጅግም ከሚበዙ ፈረሶችና ሰረገሎች ጋር በመሆን ወጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህም ሰራዊታቸውን ሁሉ እጅግ ብዙ ከሆኑ ፈረሶችና ሠረገሎች ጋራ ይዘው ወጡ፤ የሰራዊቱም ብዛት በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ከነወታደሮቻቸው ስለ መጡ፥ የሠራዊቱ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ ሆነ፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች ነበራቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ርሱ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሠራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ብዛ​ታ​ቸው እንደ ባሕር አሸዋ ሆነው ወጡ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም እጅግ ብዙ​ዎች ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነዚህም ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ከእጅግም ብዙ ፈረሰኞና ሠረገሎች ጋር ወጡ፥ በባሕር ዳርም እንዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበረ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 11:4
8 Referencias Cruzadas  

በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት እና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘሮችህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳሉ፥


አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።”


እኔ የምመክርህ፥ ቁጥሩ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛው፥ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው እስራኤል ሁሉ ወዳንተ ይሰብሰብና አንተው ራስህ ወደ ጦርነቱ ምራው፤


የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ እየበሉና እየጠጡ ዘወትር ደስ ይሰኙ ነበር።


እነኚህ በሠረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፥ እኛ ግን በአምላካችን በጌታ ስም ከፍ ከፍ እንላለን።


እነዚህም ነገሥታት ሁሉ ኃይላቸውን አስተባብረው እስራኤልን ለመውጋት መጡ፤ በማሮንም ውኃ አጠገብ በአንድ ላይ ሰፈሩ።


ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።


ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።