ዮናስ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም ሆነ እንስሳ በማቅ ይሸፈኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎች ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በመዳፋቸው ካለው ግፍ ይመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሰውም እንስሳም ማቅ ይልበስ፤ ሁሉም አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጩኽ፤ ሰዎችም ሁሉ ክፉ መንገዳቸውንና የግፍ ሥራቸውን ይተዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎችም ሆኑ እንስሶች ማቅ ይልበሱ፤ እያንዳንዱ ሰው ከልብ ወደ እግዚአብሔር ይጩኽ፤ መጥፎ ጠባዩንና የግፍ ሥራውን ይተው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎችና እንስሶችም ማቅ ይልበሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ከአለው ግፍ ይመለሱ። |
እኔስ የመረጥሁት ጾም፥ የበደልን እስራት እንድትፈቱ፥ የቀንበርንስ ጠፍር እንድትለቁ፥ የተገፉትን አርነት እንድታወጡ፥ ቀንበሩን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?
አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አስተካክሉ’ ብለህ ተናገራቸው።
እርሱም፦ ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ ጌታም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።”
በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
ስለዚህ ወደ ጌታ ጮኹ፥ እንዲህም አሉ፦ “ጌታ ሆይ! እባክህ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ እንለምንሃለን፥ ንጹሕንም ደም በእኛ ላይ አታድርግ፤ ጌታ ሆይ ደስ የሚያሰኝህን አድርገሃልና።”
የመርከቡ አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ፦ “እንዴት ትተኛለህ? ተነሥ አምላክህን ጥራ፥ ምናልባትም እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን ይሆናል” አለው።
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።
እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም።