እግዚአብሔርም ለማጥፋት ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ላከ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ ጌታ አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተፀፀተ፥ የሚያጠፋውንም መልአክ፦ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የጌታም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ዮናስ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፥ እግዚአብሔርም ራርቶ አደርግባችኋለሁ ብሎ የተናገረውን ክፉ ነገር አላደረገውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ምን እንዳደረጉና ከክፉ መንገዳቸውም እንዴት እንደ ተመለሱ ባየ ጊዜ ራራላቸው፤ በእነርሱም ላይ ሊያመጣ ያሰበውን ጥፋት አላደረገም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎች ያደረጉትንና ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህም ራርቶላቸው በእነርሱ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቅጣት አልፈጸመም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም። |
እግዚአብሔርም ለማጥፋት ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ላከ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ ጌታ አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተፀፀተ፥ የሚያጠፋውንም መልአክ፦ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የጌታም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።
ጌታም የፍርድ አምላክ ነው፤ ስለ ሆነም ጌታ ይራራላችኋልና ይታገሣል፤ ሊምራችሁም ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።
ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።”
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።
ወደ ጌታ ጸለየ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አስቀድሜ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል የፈለግሁትም ለዚህ ነበር፥ አንተ ቸርና ርኅሩኅ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ ከክፉ የምትመለስ አምላክ እንደሆንህ አውቄ ነበርና።
የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሳሉ፥ በእርሱም ላይ ይፈርዳሉ፤ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።