ዮሐንስ 20:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም “አንቺ ሴት! ስለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ፤ እኔም እወስደዋለሁ፤” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “አንቺ ሴት፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርሷም የአትክልቱ ቦታ ጠባቂ መስሏት፣ “ጌታዬ፤ አንተ ወስደኸው ከሆነ፣ እባክህ እንድወስደው፣ የት እንዳኖርኸው ንገረኝ” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ፥ “አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሺአለሽ፤ ማንንስ ትፈልጊአለሽ?” አላት። እርስዋም አትክልተኛው መስሎአት፥ “ጌታ ሆይ! አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ የት እንዳኖርከው እባክህ ንገረኝ፤ እኔ እወስደዋለሁ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስለቅስሻል? ማንንስ ትሺያለሽ?” አላት፤ እርስዋ ግን የአትክልት ቦታ ጠባቂ መስሎአት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እንዳመጣውና ሽቱ እንድቀባው ወዴት እንደ አኖርኸው ንገረኝ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም፦ “አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ” አለችው። |
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትደንግጡ፤ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው፤ እርሱ ተነሥቷል፤ እዚህ የለም፤ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ።
ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው “ሕያዉን ለምን በሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ? እርሱ እዚህ የለም፤ ይልቁንም ተነሥቶአል።
ኢየሱስም መለስ ብሎ ሲከተሉትም አይቶ “ምን ትፈልጋላችሁ?” አላቸው። እነርሱም “ረቢ!፥ (ሲተረጎም ‘መምህር ሆይ’ ማለት ነው) የምትኖረው የት ነው?” አሉት፤