ማርቆስ 16:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትደንግጡ፤ የምትፈልጉት የተሰቀለውን የናዝሬቱ ኢየሱስን ነው፤ እርሱ ተነሥቷል፤ እዚህ የለም፤ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጉታላችሁ፤ እርሱ ግን ተነሥቷል! እዚህ የለም፤ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውላችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አይዞአችሁ፥ አትደንግጡ፤ እናንተ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ተነሥቶአል፤ እዚህ የለም፤ የተቀበረበትም ቦታ ይኸውላችሁ፤ ተመልከቱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እርሱ ግን “አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፤ በዚህ የለም፤ እነሆ፥ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ። Ver Capítulo |