ኢዮብ 8:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፍህን እንደገና በሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና አፍህን በሣቅ፣ ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አንተንም በደስታ እንድትስቅና ‘እልል’ እንድትል ያደርግሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅኖችን አፍ ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮቻቸውንም ምስጋና ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አፍህን እንደ ገና ሳቅ ይሞላል፥ ከንፈሮችህንም እልልታ ይሞላል። |
እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ።
ነገር ግን፦ በሌሊት የደስታ መዝሙሮችን የሚለግስ፥ ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረን ከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም።