ኢዮብ 7:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ። ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥ እስኪ ነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተኛሁ ጊዜ ‘መቼ ነግቶ እነሣለሁ?’ እላለሁ፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ እስኪነጋም እገላበጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምተኛበት ጊዜ መቼ እነሣ ይሆን ብዬ አስባለሁ፤ ሌሊቱ ግን ይረዝምብኛል፤ እኔም እስኪነጋ ድረስ ስገላበጥ ዐድራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተኛሁም ጊዜ፦ መቼ ይነጋል? እላለሁ፤ በተነሣሁም ጊዜ ዳግመኛ መቼ ይመሻል? እላለሁ፤ ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከራን ጠገብሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? እላለሁ። ሌሊቱ ግን ይረዝማል፥ እስኪነጋ ድረስም እገለባበጣለሁ። |