እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥ የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
እንዲሁ ከንቱ ወራት ታደሉኝ፣ የጕስቍልና ሌሊቶችም ተወሰኑልኝ።
የድካም ወሮቹ ለእኔ ጥቅም የለሽ ሆኑ፤ የችግር ሌሊቶቹም ለእኔ የጭንቅ ሌሊት ሆኑብኝ።
እንዲሁ እኔ የከንቱ ወራትን ታገሥሁ፥ የፃዕርም ሌሊት ተወሰነችልኝ።
አሁን ግን አድክሞኛል፥ ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል።
በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት።
“እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደነበረው ጊዜ፥ እንደ ፊተኛው ወራት ምነው በሆንሁ!
አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥ ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።
በሞት የሚያስታውስህ የለምና፥ በሲኦልም የሚያመሰግንህ ማን ነው?
በመቃተቴ ደክሜአለሁ፥ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን በእንባ አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።
ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም መከተል ነው።