Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 7:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥ ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የምሽትን ጥላ እንደሚመኝ አገልጋይ፣ ደመወዙንም እንደሚናፍቅ ምንደኛ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እነርሱም በጥላ ሥር ለማረፍ እንደሚፈልጉ አገልጋዮችና ደመወዛቸውን ለመቀበል እንደሚጠባበቁ ሙያተኞች አይደሉምን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥ ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 7:2
11 Referencias Cruzadas  

“በባልንጀራህ ግፍ አታድርግ፥ አትቀማውም። ተቀጥሮ የሚያገለግለውን ሰው ደመወዙን እስከ ነገ ድረስ በአንተ ዘንድ አታቆይበት።


የሠራበትን ሒሣብ በዕለቱ፥ ፀሓይ ሳትጠልቅ ክፈለው፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋል። ያለበለዚያ ወደ ጌታ ይጮኽና ኃጢአት ይሆንብሃል።


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


“በእርሷ ላይ ጦርነት አዘጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ።” “ቀኑ መሽቶአልና፥ የማታውም ጥላ ረዝሞአልና ወዮልን!”


እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።


አፌን ከፈትሁ፥ አለከለክሁም፥ ወደ ትእዛዝህ ናፍቄአለሁና።


ሐሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ነፍሱ ተወስዳለችና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርሷን ስጡት።


“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?


እንዲሁ ዕጣዬ የከንቱ ወራት ሆነብኝ፥ የድካምም ሌሊት ተወሰነችልኝ።


ጌታ እግዚአብሔርም የጉሎ ተክል አበቀለ፥ ከጭንቀቱም እንድታድነው፥ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ጉሎ ተክሉ እጅግ ተደሰተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios