አንተ ብቻህን ጌታ ነህ፥ ሰማይንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርሷ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጠርህ፥ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።
ኢዮብ 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ? ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ? ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን የምትከታተል ሆይ፤ ኀጢአት ብሠራ፣ አንተን ምን አደርግሃለሁ? ለምን ዒላማህ አደረግኸኝ? ለምንስ ሸክም ሆንሁብህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውን ልብ፦ የምታውቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ እንግዲህ ምን ላደርግልህ እችላለሁ? ስለምን እኔን ለመከራ አደረግኸኝ? ስለ ምን በአንተ ላይ እንድናገር በአምሳልህ ፈጠርኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆንሁብህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ? ስለ ምን እኔን ለአንተ ዓላማ አደረግኸኝ? ስለ ምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ? |
አንተ ብቻህን ጌታ ነህ፥ ሰማይንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድርንና በእርሷ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጠርህ፥ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ።