ከበረዶ የተነሣ ደፈረሱ፥ አመዳይም ተሰወረባቸው፥
በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤
ወንዞቹ በክረምት ወራት በበረዶ ተሞልተው ይሸፈናሉ።
ያከብሩኝ የነበሩ እነዚያ፥ አሁን እንደ በረዶና እንደ ረጋ አመዳይ ሆኑብኝ፤
ድርቅና ሙቀት የበረዶውን ውኃ ያጠፋሉ፥ እንዲሁ ሲኦል በደለኞችን ታጠፋለች።
በውኑ ወደ በረዶው ቤተ መዛግብት ገብተሃልን? የበረዶውንስ ቤተ መዛግብት አይተሃልን?
በረዶስ ከማን ማኅፀን ወጣ? የሰማዩንስ አመዳይ ማን ወለደው? ውኆች እንደ ድንጋይ ጠነከሩ፥
ወንድሞቼ እንደ ፈፋ፥ እንደሚያልፍ ፈፋ ሐሰተኞች ሆኑብኝ።
ፀሐይ በተኰሰች ጊዜ ይደርቃሉ፥ በሙቀትም ጊዜ ከስፍራቸው ይጠፋሉ።
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፥ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።