ኢዮብ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋጤ ወደቀብኝ፥ እንዲሁም መንቀጥቀጥ አጥንቶቼን ሁሉ ተነዋወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍርሀትና መንቀጥቀጥ ያዘኝ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ተናወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍርሀትና መርበድበድ ይዞኝ፥ አጥንቶቼ ሁሉ እንዲንቀጠቀጡ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንጋጤና መንቀጥቀጥ ያዙኝ፤ አጥንቶቼም ሁሉ እጅግ ተነዋወጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥንቴን ሁሉ ያናወጡ ድንጋጤና መንቀጥቀጥ ወደቁብኝ። |
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።