ኢዮብ 38:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምታውቅ እንደሆነ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋም የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ? በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድርን መጠን የወሰነ ማን ነው? በእርሱዋ ላይስ የመለኪያ መስመሮችን የዘረጋ ማን እንደ ሆነ ታውቃለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብታውቅ መስፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድን የዘረጋ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብታውቅስ መሠፈሪያዋን የወሰነ፥ በላይዋስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው? |
ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ሊያደርጋቸው፥ የክብርንም ዙፋን ሊያወርሳቸው፥ እርሱ ድኾችን ከትቢያ፥ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ የምድር መሠረቶች የጌታ ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አኖረ።