የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።
ኢዮብ 38:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ እንደ ጎበዝ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ታሳውቀኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስቲ በፊቴ እንደ ወንድ ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም መልስልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። |
የጌታም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድርጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር።