የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእርሷም በደለኞች ይናወጡ ዘንድ፥
በዚህም የምድርን ዳርቻ ይዞ፣ ክፉዎችን ከላይዋ እንዲያራግፍ አድርገሃልን?
ንጋት በምድር ላይ ብርሃን እንዲያሳይ፥ ክፉ ሰዎችንም ከተደበቁበት ቦታ እንዲያጋልጥ ትእዛዝ ሰጥተህ ታውቃለህን?
የምድርን ዳርቻ ይይዝ ዘንድ፥ ከእርስዋም ኃጥኣንን ያናውጥ ዘንድ።
እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
ሥራቸውን ያውቃል፥ በሌሊት ይገለባብጣቸዋል፤ እነርሱም ይደቃሉ።
ሰዎች እያዩ እንደ ክፉዎች ይመታቸዋል፥
እርሱ በደለኛን በሕይወት አይጠብቅም፥ ለችግረኞች ግን ይፈርዳል።
መብረቁንም ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥ ወደ ምድርም ዳርቻ ይሰድዳል።
በውኑ ከተወለድህ ጀምሮ ማለዳን አዝዘህ ታውቃለህን? ለወገግታም ስፍራውን አስታውቀኸዋልን?
ጭቃ ከማኅተም በታች እንደሚለወጥ እንዲሁም እርሱ ይለወጣል፥ ፍጥረትም ሁሉ እንደ ልብስ ተቀልሞአል።
ኀጥኣን ከምድር ይጥፉ፥ ዓመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ። ሃሌ ሉያ።
ሙሴም እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፥ ባሕሩም ማለዳ ወደ መፍሰሱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ተመለሰ፤ ግብፃውያንም ከእርሱ ሸሹ፥ ጌታም ግብፃውያንን በባሕሩ መካከል ጣላቸው።