ኢዮብ 36:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም ሰዎች የዘመሩለትን ሥራውን ማክበርን አስታውስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣ የርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ሁልጊዜ በሚሠራው ሥራ በመዝሙር እንደሚያመሰግኑት። አንተም የእርሱን ሥራ በመዝሙር አመስግን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎች ሊሠሩት ከሞከሩት በላይ፥ ሥራው ታላቅ እንደ ሆነ አስብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች የዘመሩትን ሥራውን ታከብር ዘንድ አስብ። |
በዚያን ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህንን መዝሙር ለጌታ ዘመሩ፥ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለጌታ እዘምራለሁ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ፥ ጌታ አምላካችሁ ከሰማይ በታች ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸውን፥ ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም፥ የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ፥ በመሳት እንዳትሰግዱላቸውና እንዳታመልኳቸው ተጠንቀቁ።
“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።