ኢዮብ 36:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማነው መንገዱን የሚያሳየው? ወይስ፦ ‘ተሳስተሃል’ የሚለው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን መንገድ የሚመራው፣ ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ይህን አድርግ’ ብሎ የሚያዘው፥ ወይም ‘ክፉ ሥራ ሠርተሃል’ ብሎ የሚወቅሰው ማነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራውንስ የሚመረምር ማን ነው? ወይስ፦ ክፉ ሠርተሃል የሚለው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዱን ማን አዘዘለት? ወይስ፦ ኃጢአትን ሠርተሃል የሚለው ማን ነው? |
ነገር ግን ዐመፃችን የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያጎላ ከሆነ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በቁጣ ቢቀጣን ትክክል አይደለም ሊባል ነውን? እንደ ሰው እላለሁ።