ኢዮብ 36:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን የበደለኞች ፍርድ ደረሰብህ፥ ፍርድና ብይን እንደሚይዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኗል፤ ፍርድና ብይን ይዘውሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን የበደለኛ ፍርድ ስለ ተፈረደብህ፥ ተገቢ ቅጣትህን በመቀበል ላይ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርድን ለጻድቃን አያዘገይምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን በበደለኞች ፍርድ የተሞላህ ነህ፥ ስለዚህ ፍርድና ብይን ይይዝሃል። |
ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?”
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።