ኢዮብ 36:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም አንተን ከመከራ ችግር ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ በወሰደህ ነበር፥ በማዕድህም ላይ ቅባት የሞላበት ምግብ በተዘጋጀ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአሁኑም ወቅት እግዚአብሔር የሚፈቅደው፥ አንተን ከችግር አውጥቶ ምርጥ በሆነ ምግብ ወደተሞላ ማእድ ሊመራህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን ግን ከጠላትህ አፍ አድኖሃል፥ በበታችህም ጥልቅ ባሕር፥ ፈሳሽ ምንጭም አለ፥ ማዕድህም በስብ ተሞልታ ትወርዳለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም አንተን ከመከራ ችግር ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ በወሰደህ ነበር፥ በማዕድህ ላይ የተዘጋጀውም ስብ በሞላበት ነበር። |
የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
እርሷም፦ “ውሽሞቼ ለእኔ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።