እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “በጌታ ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነውና።”
ኢዮብ 36:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልበ ደንዳኖች ግን ቁጣን ይወዳሉ፥ እርሱም ባሠራቸው ጊዜ አይጮኹም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤ በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በልባቸው እግዚአብሔርን የሚክዱ ዘወትር እንደ ተቈጡ ይኖራሉ፥ ሲቀጣቸው እንኳ ይቅርታ ለማግኘት አይጸልዩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ግብዞች ግን በልባቸው ቍጣን ያዘጋጃሉ፤ እርሱም ባሰራቸው ጊዜ አይጮኹም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዝንጉዎች ግን ቍጣን ያዘጋጃሉ፥ እርሱም ባሰራቸው ጊዜ አይጮኹም። |
እነርሱም እንዲህ አሉአቸው፦ “በጌታ ፊት በእኛ ላይ በደል ታመጡብናላችሁና፥ ኃጢአታችንንና በደላችንን ታበዙብናላችሁና የተማረኩትን ወደዚህ አታግቡ፤ በደላችን ታላቅ ነውና፥ የመቅሰፍቱም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነውና።”