ኢዮብ 35:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፋትህ የሚጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጆች ብቻ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአት ብትሠራ የምትጐዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ነው፤ መልካም ሥራ ብትሠራ፥ የምትጠቅመው ሰውን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጎዳዋል፤ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል። |
እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።
አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።