ኢዮብ 34:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሏልና፥ ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ ሹፈትን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዝን እንደ ውሃ የሚጠጣት፣ እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንደ ኢዮብ በእግዚአብሔር ላይ የሚያፌዝ ሰው ከቶ ይገኛልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መሣለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣት፥ እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮብም፦ በእግዚአብሔር መደሰት ለሰው ምንም አይጠቅምም ብሎአልና ከበደለኞች ጋር የሚተባበር፥ ክፉ ከሚያደርጉስ ጋር የሚሄድ፥ መሳለቅን እንደ ውኃ የሚጠጣት እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው? |
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፥ በልቡ ራሱን በመባረክ፥ ‘ምንም እንኳ እንደ ልቤ ደንዳናነት ብሄድ ሰላም አለኝ’ ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።