ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።
ኢዮብ 34:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፥ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማየት ያልቻልሁትን አስተምረኝ፤ ኀጢአት ሠርቼ እንደ ሆነም፣ ደግሜ አልሠራም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራሁት ኃጢአት የትኛው እንደ ሆነ አስተምረኝ፤ በድዬም ከሆነ፥ ዳግመኛ አልሠራም’ ያለው ሰው አለን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ራሴ አያለሁ፥ ኀጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰትንም ተናግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እንዳልሠራ አንተ አሳየኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማላየውን ነገር አንተ አስተምረኝ፥ ኃጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ደግሜ አልሠራም የሚለው ማን ነው? |
ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።
አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ አንድም ሰው፦ ‘ምን አድርጌአለሁ?’ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ጦርነትም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።
ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፤ እንደ አትክልት ስፍራ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይንም ተክል ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
በለዓምም የጌታን መልአክ እንዲህ አለው፦ “ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ አንተ በመንገድ ላይ ልትቃወመኝ መቆምክን አላወቅሁም፤ እንግዲህም ይህ አሁን በፊትህ ክፉ የሆነ ነገር ቢሆን እመለሳለሁ።”