ኢዮብ 34:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎች እያዩ እንደ ክፉዎች ይመታቸዋል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ክፋታቸውም፣ በሰው ሁሉ ፊት ይቀጣቸዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሠሩት ዐመፃ ምክንያት ኃጢአተኞችን በሰው ፊት ይቀጣቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣንን ያጠፋቸዋል፥ ጻድቃን ግን በፊቱ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎች እያዩ እንደ ክፉዎች ይመታቸዋል፥ |
ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።
ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፥ በብዙ ሴቶችም ፊት በላይሽ ፍርድን ያደርጉብሻል፥ አመንዝራነትሽን አስተውሻለሁ፥ ከእንግዲህም በኋላ ዋጋ አትሰጪም።
ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።