ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
ኢዮብ 33:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔም እንዳንተ ከጭቃ የተቀረጽሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት እኔም እንደ አንተው ነኝ፤ የተፈጠርሁትም ደግሞ ከዐፈር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ እኔና አንተ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ነን፤ እኔም የተፈጠርኩት ከጭቃ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተፈጠርህ ነህ፥ የሁላችንም ተፈጥሮ ከዚያው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት እኔ እንደ አንተ ነኝ፥ እኔ ደግሞ ከጭቃ የተፈጠርሁ ነኝ። |
ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።
ስለዚህ እግዚአብሔር ጥሪውን የሚያቀርበው በእኛ በኩል በመሆኑ፥ እኛ ለክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ስለ ክርስቶስ ሆነን “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ” ብለን እንለምናለን።