ኢዮብ 33:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየራራለት፦ እሱን መታደጊያ ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ መቃብር እንዳይወርድ አድነው ቢለው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰውየውም በመራራት፣ ‘ቤዛ አግኝቼለታለሁና፣ ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልአኩም አዝኖለት ‘ቤዛ ያገኘሁለት ስለ ሆነ፥ ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥ ተወው!’ ብሎ ሞትን ያዘዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞት እንዳይጠፋ ይጠብቀዋል፥ ሰውነቱንም እንደ ግድግዳ ምርግ ያድሳታል። አጥንቶቹንም በመቅን ይሞላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየራራለት፦ ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው ቢለው፥ |
እርሱም እንዲህ አለው፦ “እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለሁ የጌታንም ስም በፊትህ አውጃለሁ፤ ይቅር የምለውን ይቅር እላለሁ፥ የምምረውን እምራለሁ።”
በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ።
አሦር አያድነንም፤ በፈረስ ላይ አንቀመጥም፤ ድሀ አደጉም በአንተ ዘንድ ምሕረትን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ ለእጆቻችን ሥራ፦ ‘አምላኮቻችን’ ናችሁ አንላቸውም።”