ኢዮብ 31:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይፋ ድጋፍ አለኝ ብዬ፥ በወላጅ አልባ ላይ እጄን አንሥቼ የቃታሁ እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአደባባይ ተሰሚነት አለኝ ብዬ፣ በድኻ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍርድ ሸንጎ ተሰሚነት ያለኝ መሆኔን በማወቄ በሙት ልጅ ላይ እጄን አንሥቼ አላውቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ረዳት እንዳለኝ ተማምኜ በድሃአደጉ ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበሩ ረዳት ስላየሁ፥ በድሀ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥ |
ወፍረዋል ሰብተዋልም፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆንላቸው አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግርተኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።