በፀሐይ ሳይሆን በትካዜ ጠቁሬ ሄድሁ፥ በጉባኤም መካከል ቆሜ ጮኽሁ።
በፀሓይ አይደለም እንጂ፣ ጠቋቍሬ እዞራለሁ፤ በጉባኤ መካከል ቆሜ ለርዳታ እጮኻለሁ።
ሰውነቴ በፀሐይ ቃጠሎ ሳይሆን በሐዘን ጠቈረ፤ በአደባባይም መካከል ቆሜ ርዳታ እጠይቃለሁ።
በጠባቡ ሄድሁ፥ የሚያሰፋልኝም አጣሁ፥ በጉባኤም መካከል ቆሜ እጮኻለሁ።
ያለ ፀሐይ በትካዜ ሄድሁ፥ በጉባኤም መካከል ቆሜ ጮኽሁ።
እነሆ፥ ስለ ተደረገብኝ ግፍ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፥ ድረሱልኝ ብዬ ብጣራ ፍርድ የለኝም።
ስለዚህ መሰንቆዬ ለኀዘን፥ እምቢልታዬም ለሚያለቅሱ መሳርያ ሆነ።”
ከአላዋቂነቴ የተነሣ ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም፥
ጌታ በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፥ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።
አንተ አምላኬ ኃይሌም፥ ለምን ትተወኛለህ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ?