ኢዮብ 30:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለተጨነቁት አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራ ውስጥ ላሉት አላለቀስሁምን? ለድኾችስ ነፍሴ አላዘነችምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለተቸገሩ ሰዎች አላለቀስኩምን? ለድኾችስ አልተጨነቅኹምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ረዳት ለሌለው ሰው አለቀስሁ የተቸገረ ሰውን ባየሁ ጊዜ ጮኽሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጭንቅ ቀን ላገኘው ሰው አላለቀስሁምን? ለችግረኛስ ነፍሴ አላዘነችምን? |
ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።