ኢዮብ 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ክፉዎች አስቸጋሪነታቸው ይቀራል፤ በአድካሚ ሥራም የኖሩ ያርፋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥኣን በዚያ በቍጣው መቅሠፍት ይቃጠላሉ፤ በዚያም በሥጋቸው የተጨነቁት ያርፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉዎች በዚያ መናደዳቸውን ይተዋሉ፥ በዚያም ደካሞች ያርፋሉ። |
ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ከወዲሁ ጠፍቶአል፥ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘለዓለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም።
ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ። “ይህንን ጻፍ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።” መንፈስም “አዎን! ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸው ይከተላቸዋልና፤” ይላል።
ገና ጌታ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል፤ አንተና ልጆችህም ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”