ኢዮብ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማኅፀን ሳለሁ ስለምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ስለምን ፈጥኜ አልጠፋሁም? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምነው ገና ስወለድ በጠፋሁ! ምነው ከማሕፀን ስወጣ በሞትሁ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምነው በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ ውሃ ሆኜ በቀረሁ! ከማሕፀን ስወጣስ ለምን አልጠፋሁም? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ወዲያውኑ ስለ ምን አልጠፋሁም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም? |
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።