ኢዮብ 27:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሱ የተረፉትም በቸነፈር ይቀበራሉ፥ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተረፉለትም በመቅሠፍት ዐልቀው ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ የተረፉትም በበሽታ ያልቃሉ፤ መበለቶቻቸው እንኳ አያለቅሱላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱም የቀሩት ፈጽመው ይሞታሉ። ለመበለቶቻቸውም የሚያዝንላቸው የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርሱም የቀሩት በቸነፈር ይቀበራሉ፥ መበለቶቻቸውም አያለቅሱም። |
ስለዚህ ጌታ ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ “ ‘ወንድሜ ሆይ! ወዮ! እህቴ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም፦ ‘ጌታ ሆይ! ወዮ! ግርማዊነቱ ሆይ! ወዮ!’ እያሉ አያለቅሱለትም።
መጠምጠሚያችሁ በራሳችሁ ላይ፥ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ ዋይ አትሉም ወይም አታለቅሱም፤ በኃጢአታችሁ ትመነምናላችሁ፥ እርስ በእርሳችሁም ታለቅሳላችሁ።