ኢዮብ 27:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ ቢበዙ በሰይፍ ይሞታሉ፥ ዘሩም በቂ እንጀራ ከቶ አያገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቹ የቱንም ያህል ቢበዙም ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ ዘሩም ጠግቦ አያድርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹ ቢበዙ በጦርነት ያልቃሉ፤ ዘሮቹም ምግብ አጥተው ይራባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቹ ቢበዙ ለጥፋት ይሆናሉ፤ ቢያድጉም ለማኞች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይሆናሉ፥ ዘሩም እንጀራን አይጠግብም። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።
ጠግበው የነበሩ አጥተው ለእንጀራ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን ከራብ ዐርፈዋል። መካኒቱ ሰባት ወለደች፥ ብዙ የወለደችው ግን ብቻዋን ቀረች።