ኢዮብ 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ያስቀጥላል፥ እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር ኀያላንን በኀይሉ ጐትቶ ይጥላል፤ ቢደላደሉም የሕይወት ዋስትና የላቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እግዚአብሔር በኀይሉ በሥልጣን ላይ ያሉትን ሰዎች ያስወግዳቸዋል። ኑሮአቸው የተሳካ ቢመስልም እንኳ የመኖር ዋስትና የላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ረዳት የሌላቸውን በቍጣው አጠፋቸው። እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በኃይሉ ኃያላንን ይስባል፥ እርሱም በተነሣ ጊዜ ሰው በሕይወቱ አይታመንም። |