እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርሷ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጇን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጐኔ አስተኛችው።
ኢዮብ 24:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ በብርሃን ላይ የሚያምፁ ናቸው፥ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በብርሃን ላይ የሚያምፁ፣ ጐዳናውን የማያውቁ፣ በመንገዱም የማይጸኑ አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ብርሃንን የሚጠሉ ሰዎች አሉ፤ ብርሃንም ምን እንደ ሆነ ስለማያውቁ የብርሃንን መንገድ አይከተሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? በምድር ላይ ሳሉ አላስተዋሉም፥ የቅንነት መንገድንም አላዩም። በአደባባይዋም አልሄዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ በብርሃን ላይ የሚያምፁ ናቸው፥ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም። |
እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርሷ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጇን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጐኔ አስተኛችው።
ኢየሱስም “ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም።
እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከእራሱ አፍልቆ ነው፤ ሐሰተኛ፥ የሐሰትም አባት ነውና።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።
የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።