ኢዮብ 24:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ያቃስታሉ፥ ቁስለኞችም ለእርዳታ ይጮኻሉ፥ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሟቾች ጣር ጩኸት ከከተማዋ ይሰማል፤ የቈሰሉት ሰዎች ነፍስ ለርዳታ ይጮኻል፤ እግዚአብሔር ግን ተጠያቂዎቹን ዝም ብሏል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ሰዎች ይቃትታሉ፤ የቈሰሉትም ሰዎች ርዳታ በመጠየቅ ይጮኻሉ። እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ላይ የተሠራውን ግፍ አልተመለከተም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሆችን ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው አባረሩአቸው የሕፃናትንም ነፍስ እጅግ አስጮሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው ይባረራሉ፥ የልጆችም ነፍስ ለእርዳታ ትጮኻለች፥ እግዚአብሔር ግን ስንፍናቸውን አይመለከትም። |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል ጌታ፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፥ ይላል ጌታ፥ ስሜም ያለማቋረጥ በየእለቱ ቀኑን ሙሉ ይሰደባል።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
በቃላችሁ ጌታን አሰልችታችሁታል። እናንተም፦ እርሱን ያሰለቸነው በምንድን ነው? ትላላችሁ። “ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ፊት መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ የት አለ?” በማለታችሁ ነው።