La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በፊቱ አቤቱታዬን አቀርብ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጕዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤ አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቤቱታዬን በፊቱ አሰማ ነበር፤ የመከላከያ መልሴንም በዝርዝር አቀርብ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሠ​ራ​ሁት ቢኖር ይነ​ግ​ረኝ ነበረ፥ ስከ​ራ​ከ​ርም አፌ ዝም አይ​ልም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በፊቱ ሙግቴን አዘጋጅ ነበር፥ አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር።

Ver Capítulo



ኢዮብ 23:4
15 Referencias Cruzadas  

አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።”


እነሆ፥ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ። ጽድቄም እንደሚገለጽ አውቃለሁ።


ነገር ግን ሁሉን ለሚችል አምላክ መናገር እፈልጋለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር ለመዋቀስ እሻለሁ።


እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!


የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደሆነ አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም አስተውል ነበር።


እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና ለርሱ የምንለውን አስታውቀን።


“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”


አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።


አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።


አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።