ኢዮብ 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥ የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃል፤ የድኻ አደጎችንም ክንድ ሰብረሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤ የሙት ልጆችንም መተዳደሪያ አጥፍተሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መበለቶችን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል፥ ድሃአደጎችንም አስጨንቀሃቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መበለቲቱን አንዳች አልባ ሰድደሃታል፥ የድሀ አደጎችም ክንድ ተሰብሮአል። |
ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ነኝ፥ የበረታችውንና የተሰበረችውን ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ እጥለዋለሁ።
ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።