ክፋትህስ ብዙ አይደለምን? ለዐመፅህም ወሰን የለውም።
ክፋትህ ታላቅ፣ ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
ይህ ሁሉ የደረሰብህ ክፋትህ ስለ በዛና ኃጢአትህም ወሰን የሌለው ስለ ሆነ አይደለምን?
“ክፋትህስ የበዛ አይደለምን? ኀጢአትህስ ቍጥር የሌለው አይደለምን?
ክፋትህስ የበዛ አይደለምን? ለኃጢአትህም ፍጻሜ የላትም።
የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”
“እነሆ፥ ሐሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ሰዎች መመለስን ተዉ።
ከራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ የኤሊሁ ቁጣ ነደደ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው።
እንዲሁም በኢዮብ ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላላገኙ በሦስቱ ባልንጀሮቹ ላይ ተቈጣ።
አንተ ግን የበደለኞች ፍርድ ደረሰብህ፥ ፍርድና ብይን እንደሚይዛቸው።
አገልጋይህ ደግሞ ይጠብቀዋል፥ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።